ጉርሻ – መንጃ ፈቃድ ለሚመልሱ

0
11

አውሮፓዊቷ ሀገር ማልታ የተስተዋለባትን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ለመፍታት መንጃ ፈቃዳቸውን በፈቃዳኝነት ለአምስት ዓመታት የቆይታ ጊዜ ለሚመልሱ አሽከርካሪዎች ለእያንዳንዳቸው ሃያ ዘጠኝ ሺህ ዶላር ለመስጠት ማቀዷን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብብል፡፡

በማልታ የትራፊክ መጨናነቅ የማያቋርጥ ችግር ሆኖ በመገኘቱ በመፍትሄነት ባለስልጣናቱ “የመንጃ ፈቀድ ማስረከቢያ” የተሰኘ የችግር ማቃለያ ዕቅድ ማዘጋጀታቸው ተጠቁሟል፤ በድረ ገጹ፡፡

የትንስፖርት ሚኒስትሩ ክሪስ ቦኔት እንደገለጹት የመንጃ ፈቃድ ማስረከቢያ ዕቅዱ የአሽከርካሪዎችን ቁጥር ለመቀነስ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቀሚትን ለማበረታታት፣ የትራፊክ መጨናነቅን በመግታት በድምር ውጤቱ የብክለት መጠን መቀነስን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡

በተነደፈው ዕቅድም አሽከርካሪዎች የመንጃ ፈቃዳቸውን ለአምስት ዓመታት ሲያስረክቡ ለእያንዳንደቸው በየዓመቱ  28 ሺህ 650 ዶላር ወይም 25 ሺህ ዩሮ እንደሚሰጥ ይፋ ሆኗል፡፡

ዕቅዱ ይፋ በሆነበት ሰሞን በርካታ ወጣት አሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃዳቸውን ለመመለስ ፍላጐት ማሳያታቸውንም አረጋግጠዋል፤ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ፡፡

የማበረታቻ ክፍያው ፈቃድ ለሚያስረክቡ የሚሰጠው በየዓመቱ ተከፋፍሎ ሲሆን ፈቃድ መልሰው ሃሳባቸውን በመካከሉ የሚቀይሩ የወሰዱት ተሰልቶ እንደሚመለስላቸው ነው ድረ ገጹ ያስነበበው፡፡ ለዕቅዱ ማስፈፀሚያ አገሪቱ አምስት ሚሊዬን ዮሮ ዓመታዊ በጀት መመደቧ እና አንድ ሺህ ፈቃደኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዷ ነው ለንባብ የበቃው፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here