በሰ/ጎጃም ዞን በአዴት ከተማ አስተዳደር የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የዘር ማበጠሪያ ማሽን ከአሰላ አዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በሎቬድ መኪና ማስመጣት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም አካል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችል፡፡
- የባለቤትነት ወይም የተሸከርካሪ ሊብሬ ማቅረብ የሚችል።
- የግዥው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻችው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የዘር ማበጠሪያ ማሽኑን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። 16ኛ ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ስም እና አድራሻ የሚገልፅ (ህጋዊ ወኪል) የተፈረመበት ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ አለባቸው ።
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሲፒኦ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከክፍሉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-338-11-66 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት