የምሥራቅ ጐጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለዞን ፖሊሲ መምሪያ እና ደብረ ማርቆስ አድማ መከላከል ፖሊስ ጽ/ቤት አገልግሎት ለሚሰጡ እቃዎችን ሎት 1. የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 2. የተሸከርካሪ የወንበር ልብስ እና ሎት 3 ጀኔሪተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
- በዘርፉና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የግብር መክፈያ መለያቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሪዲት ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለመ/ቤ /ገንዘብ ያዥ በመሂ1 ገቢ ማድረግ አለባቸዉ በእያንዳንዱ ሎት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ያላነሰ ከሁለት በመቶ ያልበለጠ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሠነድ በጥንቃቄ በማሸግ የግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱን የተጫራቹን ስምና አድራሻ በመፃፍ በማህተምና ፊርማ አስደግፎ ለግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ ሠነዱን መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የእቃዉን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሠነዱን ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ሠነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 መገኘት በፈለጉ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ/ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
- አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል ይዞ ያሸነፈበትን /አገልግሎት/ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ 1ኛ ደረጃ የሆነውን በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት መስጠት አለበት፡፡ ከስፔስፊኬሽኑ ውጭ የሚሰጥ አገልግሎት የማንቀበል መሆኑ ታውቆ ለሚደርስበት ኪሣራ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ወይም ዝግ ከሆነ ስዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ዉድድሩ የሚካሄደዉ ሎት (ጥቅል) ዋጋ ሲሆን ሁሉንም አገልግሎትና ሽያጭ ዋጋ መሙላት አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 21 46 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የምሥራቅ ጐጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ