በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሻሁራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታዎችን በመሬት ሊዝ ጨረታ መመሪያ መሰረት ለተጫራቾች አወዳድሮ ማስተላለፍና ማልማት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች በከተማው ፕላን መሰረት በአገልግሎት አይነት የተዘጋጁትን ቦታዎች ማለትም፡-
- ድርጅት = ባለ 500 ካ/ሜ ብዛት 1 ስፋት 500 ካ/ሜ
- ድርጅት = ባለ5 ካ/ሜ ብዛት 1 ስፋት 262.5 ካ/ሜ
- ቅይጥ = ባለ 260 ካሜ ብዛት 1 ስፋት 260 ካ/ሜ
- ቅይጥ = ባለ 230 ካ/ሜ ብዛት 1 ስፋት 230 ካ/ሜ
- ቅይጥ = ባለ 352 ካሜ ብዛት 1 ስፋት 352 ካ/ሜ
- መኖሪያ = ባለ 150 ካሜ ብዛት 2 ስፋት 300 ካ/ሜ
- መኖሪያ = ባለ 170 ካ/ሜ ብዛት 1 ስፋት 170 ካ/ሜ
- መኖሪያ ባለ 190 ካ/ሜ ብዛት 1 ስፋት 190 ካ/ሜ
- የጥቃቅን እና አነስተኛ ማምረቻዎች = ባለ 240 ካ/ሜ ብዛት 2 ስፋት 480 ካ/ሜ
- የጥቃቅን እና አነስተኛ ማምረቻዎች = ባለ5 ካ/ሜ ብዛት 1 ስፋት 232.5 ካ/ሜ
- የጥቃቅን እና አነስተኛ ማምረቻዎች = ባለ5 ካሜ ብዛት 1 ስፋት 237.5 ካ/ሜ
ጠቅላላ ብዛት = 13 ጠቅላላ ስፋት 3,214.5 ካሜ የተዘጋጁትን የከተማ ቦታዎችን ለተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድረን ማስተላለፍ ስለፈለግን ሰነድ ገዝተው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንጠይቃለን፡፡
የሻሁራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት