መብረቅ  የሚያለመልመዉ

0
155

በመብረቅ የሚመቱ አበዛኞዎቹ ዛፎች ይደርቃሉ ወይም የሚተርፍ ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ ሆኖም ከነዚህ በተለየ ለረዢም ዓመታት በተደረገ ጥረት ተመራማሪዎች ከመብረቅ ጥቃት መትረፍ ብቻ ሳይሆን በጥቃቱ የሚለመልም ዝርያ ማግኘታቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ በሚያዚያ ወር መግቢያ ለንባብ አብቅቶታል፡፡

ላለፉት ዘመናት መብረቅ በዛፎች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚያሳርፍ ነበር በተመራማሪዎች መግባባት ላይ የተደረሰው፡፡ ነገር ግን በቅርቡ በአማዞን ደን የአዳዲስ ዝርያዎች መረጃ ሲሰበሰብ የመብረቅ ምትን የሚቋቋሙ ዝርያዎች ተገኝተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥረት “ዲፕቴይክስ አሊፌራ” የተሰኘው የመብረቅ ጥቃትን መቋቋም ብቻ ሳይሆን በጥቃቱ የሚለመልም መሆኑን ተገንዝበዋል፡፡

ተመራማሪዎች “ዲፕቴይክስ ኦሊፌራ” በዝግመት ለውጥ መብረቅን ለመሳብ የቻለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የዛፉ ዝርያ በዙሪያው ከሚገኙት በቁመቱ ረዝሞ እንደሚበልጥም ነው ያረጋገጡት፡፡ የቁመቱ መርዘም በስሩ ከሚገኙት ከፍ ብሎ መብረቅ ሲመጣ ያን የተወረወረውን ኃይል ወደስሩ አስተላልፎ በስሩ የሚገኙ ውኃ እና ንጥረ ነገሮችን የሚሻሙት እንዲወድሙ ወይም እንዲደርቁ የሚያደርግ መሆኑን ነው በክትትላቸው ያረጋገጡት – ተመራማሪዎቹ፡፡

“ዲኘቴይክስ ኦሊፌራ” በአማካይ 300 ዓመታት እንደሚቆይ ያረጋገጡት ተመራማሪዎቹ ከእነዚህ ዓመታት በዓማካይ በየ56 ዓመታት በመብረቅ ይመታል፡፡

ተመራማሪዎቹ እስከአሁን ከመብረቅ ምት እንዴት እንደሚተርፍ በውል  ሳይንሳዊ ትንታኔ አልሰጡም፡፡ ይሁን እንጂ የዛፉ ዝርያ የመብረቅ ምቱን በቅጠሎቹ መካከል አሳልፎ ወደ ስሩ ወይም ከጥጉ ወደ ሚገኙት እንደሚያስተላልፉ ነው የተገነዘቡት፤

“ዲፕቴይክስ ኦሊፌራ” በመብረቅ ተመቶ መትረፉ ብቻ ሳይሆን  በስሩ የሚገኙ ዛፎች ሲወድሙ በብቸኝነት  ንጥረ ነገሮችን በመሰብሰብ እንደሚፋፋ እና እንደሚለመልም ነው የድረ ገጹ ጽሁፍ ያመላከተው፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here