በምሥራቅ ጎጃም ዞን ገን/ኢ/ል/ት/መምሪያ የደ/ጥ/ግ/ወረዳ ገን/ኢ/ል/ጽ/ቤት በደባይ ጥላት ግን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የቁይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተቋርጦ የቆየውን G+2 ባለ 15 ክፍል የመማሪያ ህንፃ ግንባታ በአልማ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች
- ከላይ በተጠቀሱት የሥራ ዘርፍ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማስረጃዎችን ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገነባውን ግንባታ የያዘ ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 ድረስ መውሰድ ይኖርባቸውል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እስከ 22ተኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ለግንባታው የሚያስፈልገው የሙያ ብቃት ደረጃ 5Bc-Gc እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈው ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም /በሲፒኦ/ ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡ ነገር ግን የሞላው ዋጋ ከመሀንዲስ ግምቱ 25 በመቶ ዝቅ ብሎ ለሞላ ተጫራች ሊያያዝ የሚችለው የውል ማስከበሪያ 25 በመቶ ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ የሰጠ መሆኑ ታውቆ ለሁሉም አይተሞች በዋጋ መሞላት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በስም በታሸገ ፖስታ በደ/ጥ/ግ/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወተር በሥራ ስዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22 ተኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ጥ/ግ/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ22 ተኛው ቀን 3፡30 ላይ ታሽጎ 4፡00 ጀምሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ላይ በበዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 257 02 57 /01 43 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገን/ኢ/ል/ጽ/ቤት