በአፈፃፀም ከሣሽ አቶ ጠብቀው ታፈረ እና በአፈፃፀም ተከሣሽ አቶ ታደሰ መልካም መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በአፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ በማራኪ ቀበሌ አስተዳደር በካርታ ቁጥር አፄ ቴ/11811/2016 በወ/ሮ ራሄል አየለ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን በ150 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውን የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋው ብር 7‚539‚652.4/ሰባት ሚሊየን አምስት መቶ ሰላሣ ሰጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሃምሣ ሁለት ብር ከ4/100 ሣንቲም ሆኖ ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ መጫረት የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በስዓቱና በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የመጨረሻ አሸናፊው ያሸነፈበትን ¼ ኛውን ወዲያውን በሞዴል 85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ ያሣውቃል፡፡
የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ከፍ/ፍ/ቤት