ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
120

በምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የምዕ/ጎ/ዞን ጤና መምሪያ ለሰከላ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ፣ለደጋዳሞት ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ፣ለቋሪት ወረዳ ጤና ጽ/ቤት እንዲሁም በ3ቱ ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ የቀበሌ ጤና ጣቢያዎች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 ያገር ውስጥ ፈርኒቸር ፣ሎት 2 ህትመት ፣ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት 4 የጽዳት እቃ ፣ሎት 5 የቤትና የቢሮ እቃ ፣ሎት 6 መጋረጃና ጠረጴዛ ልብስ ፣ሎት 7 ህንፃ መሳሪያ እና ሎት 8 የኤሌክትሪክ እቃ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ አግባብነት ያለው  የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ መሰረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ሲሆን በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው ዕቃዎች ለአንድም ዕቃ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 በመሄድ ለሁሉም ሎቶች የመጫረቻ ሰነድ እያንዳንዳቸውን ብር 100 /አንድ መቶ ብር/  ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብ/ መምሪያ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ክብ ማህተም ፖስታው ላይ በማድረግ ምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ትብ/መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ  በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ትብ/መምሪያ በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00  ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ እና እቃዎችን ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብ/መምሪያ ንብረት ክፍል  ድረስ የማጓጓዣ ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡ የተሻለ አማራጭ ካገኘም ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
  14. ተጫራቾች የዕቃዎችን ናሙና ምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብና ኢ/ትብ/መምሪያ ቢ/ቁ 26 ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
  15. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢ/ትብ/መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 05 87 75 08 95 በመደወል ማብራሪያ መቀበል ይችላሉ፡፡

የምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብ/ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here