አማራ አፍ ኤም ባሕር ዳር 96.9 23ኛ  ዓመቱን አከበረ

0
135

የአማራ ክልል ን የመረጃ ፍላጎት ለማርካት ተስፋ ሰንቆ በ1994 ዓ.ም የተቋቋመው አማራ ኤፍ ኤም ባህር ዳር 96.9 የተለያዩ ፈተናዎችን ተሻግሮ 23ኛ ዓመቱን ደፍኗል ፡፡

በጥቂት የሰው ኀይል እና በውስን የስቱዲዮ ቁሳቁስ በውስን የአየር ሰዓት ስራውን በመጀመር ለልማት፤ ለመልካም አስተዳደር  እና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጉልህ ሚና አበርክቷል ፡፡

የአሚኮ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥየ እንደተናገሩት ጣቢያው 23ኛ ዓመቱን ባከበረበት ወቅት በሰጡት አስተያየት የያኔው ባህርዳር ኤፍ ኤም ባህርዳር 96.9 ውስን የአየር ሽፋን እንደነበረው በመግለጽ በአሁኑ ወቅት ሽፋኑን ማሳደግ ተችሏል፤ይህን ውስንነቱን ለማሳደግ ለዓመታት በተሰራ ስራ በአሁኑ ወቅት ሽፋኑንም የአየር ሰዓቱንም  ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

አቶ ሙሉቀን ጨምረው እንደተናገሩት ልምድ ባላቸው እና ታታሪ  ሰራተኞች ጣቢያው ተጽእኖ ፈጣሪ መሆን ችሏል፤ በቀጣይ ጣቢያው ተመራጭ እንዲሆን የተሻለ ስራ ይሰራል ብለዋል፤ አሁን ባለበት ደረጃ አማርኛ ቋንቋ የሚሰሙ ሁሉ አድማጮች ጣቢያውን ማድመጥ የሚችሉበትን ስራ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡

የአማራ ኤፍ ኤም ባህር ዳር 96.9 ዋና አዘጋጅ ብርሀኑ ክንዱ በበኩላቸው ጣቢው በየጊዜው የማሻሻያ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀው ጥራት ያላቸው ፕሮግራሞችን ይዞ ወደ አድማጭ ለመቅረብ  እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ብርሀኑ አክለውም በዚህ 23ኛ ዓመታችንን ስናከብር ከአድማጮች ገንቢ አስተያየት ለማግኘት እና እንደገና አስተካክለን ለመቅረብ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ከአንገፋ ጋዜጠኞች መካከል የስፖርት ዋና አዘጋጅ የሆነው ኃይሌ አበራ እንደተናገረው ጣቢያው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ እንዳሳየ ተናግሯል፡፡ ጋዜጠኛ ዘላለም ጌታቸው በበኩሏ በጣም ተደራሽ መሆን የቻለ ከክልል አልፎም በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ተደራሽ  ኆናል ብለዋል፡፡ጣቢያዉ በ23 ዓመት ጉዞውም ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡

(መሰረት ቸኮል)

በኲር የሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here