የከተማ ቦታ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
61

የሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በ2017 በጀት አመት 1ኛ ዙር ጨረታ የድርጅት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለአሸናፊዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ከ04/09/2017 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዘር መረጃና የጨረታ ሰነድ ሀሙሲት ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት የማይመለስ ብር ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ብቻ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን በ11፡00 የሚዘጋ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ቦታው በሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ግቢ ይሆናል፡፡
  5. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከትና በስልክ ቁጥር 058 443 00 62 ወይም 058 443 04 94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሀሙሲት ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here