በምዕራብ ጎጃም ዞን በደጋ ዳሞት ወረዳ የፈረስ ቤት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት አመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ሎት2 ወረቀትና የወረቀት ውጤቶችን እና ሎት 3 የህንጻ መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የሚያቀርቡት እቃ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዙት እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለእቃዎቹ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በፈረስ ቤት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን/ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፈረስ ቤት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የመክፈቻ ጊዜው አይራዘምም፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈውን እቃ ከተቋሙ ንብረት ክፍል ማድረስ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ውድድሩ የሚካሄደው በሎት /ጥቅል ዋጋ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር / ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በማስታወቂያ ያልተገለጸ ካለ በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ከሎት ውስጥ አንዱን እቃ ካልሞሉ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾቹ በሰነዱ ላይ የድርጅቱን ስም ፣ማህተም ፣ፊርማ እና አድራሻ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ውሉን ከወሰደበት ቀን ጀምሮ እቃዎችን በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በፈረስ ቤት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመቅረብ ወይም በ09 12 79 78 12 /09 20 77 22 08 /09 10 67 87 33 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የፈረስ ቤት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ