የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
75

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8/1 መሰረት በ2017 በጀት አመት ለ3ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ብዛት 20 ፣ለድርጅት 5 እና በማኒፋክቸሪግ ብዛት 3  አጠቃላይ 28 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተሳሰፍ ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመሰስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 3 ማስገዛት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ10 ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታ የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልሆነም ተወካዮችም ሆነ ግለሰቦቹ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በነ/መ/ቀበሌ 03 ኢ/ል/ከ/አገ/ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  5. ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  6. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በጽ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 01 92 ወይም 058 445 13 60 ደውለው ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ሌሌች ተጨማሪ ዝርዝር ሃሳቦችን /ህጎችን/ ከሚሸጠው ሰነድ ማገኘት ይችላሉ፡፡
  8. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here