በልብ ህመም ለሞት መዳረግን ያባባሰዉ

0
67

የግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

ለቤት ውስጥ  መገልገያዎች  የተለያዩ ኘላስቲክ ለማምረት የሚውለው ኬሚካል በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓመት ከ350 ሺህ ለሚበልጡ በልብ ህመም ከሚሞቱ ጋር እንደሚገናኝ ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት አስነብቧል፡፡

ኤንዋይዩ ግሩስማን የጤና ትምህርት ቤት  በመረጃ ምንጭነት ለንባብ እንዳበቃው በ2018 እ.አ.አ በተደረገ ጥናት ብቻ ለቤት ውስጥ ቁሳቁስ ማምረቻ ከሚውሉ ኬሚካሎች  ጋር በተገናኘ ከ365 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡

በጤና ተቋሙ ተመራማሪዎች የተመራው ቡድን በመዋቢያዎች፣ በኘላስቲክ ቱቦዎች፣ ቆሻሻ ማ  ጽጃ ወ.ዘ.ተ ለመስራት የሚውል ኬሚካል የሚያሳድረውን ተፅእኖ ፈትሿል፡፡

 

በተለይም ቡድኑ (di-2 – ethlhexyl phthalate(DEHP) በተባለው ኬሚካል ላይ ትኩረት አድርጐ አጥንቷል፡፡ ኬሚካሉ ኘላስቲክን ለስላሳ እና ተለዋዋጭ ለማድረግ የሚውል መሆኑንም ነው ተመራማሪዎቹ የጠቆሙት፡፡

ለተጠቀሰው (phthlate) ለተሰኘው ኬሚካል መጋለጥም በልብ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች የመለብለብ እና የማበጥ ተፅእኖ እንደሚያሳድር ነው የደረሱበት፡፡ ይህም ለልብ ድካም፣ የደም መፍሰስ   (ስትሮክ) የመጋለጥ አጋጣሚን ይጨምራል፡፡ በዚህም ቡድኑ ከ510 እስከ 3ነጥብ 74 ትሪሊዮን ዶላር ምጣኔ ሀብታዊ ጫና ሊያሳድር እንደሚችልም ነው ያስቀመጠው፡፡

 

በ2021 እ.አ.አ የምርምር ቡድኑ ባደገው ጥናትም በአሜሪካን በእድሜ ከ55 ዓመት በላይ ከገፉቱ 50 ሺህ ሞት ከኘላስቲክ ማለስለሻ ኬሚካል ጋር እንደሚገናኝ ነው በግኝትነት ያሰፈሩት፡፡

የምርምር ቡድኑ ከ200 አገራት መረጃ እና  የሽንት ናሙናም ሰብስቧል፤ የሞት ልኬታ ወይም ምጣኔንም መዝግቧል፡፡ በምስራቅ እስያ እና መካከለኛው የሞት ምጣኔው 42 በመቶ እና 32 በመቶ ከኘላስቲክ መስሪያ ኬሚካል ጋር እንደሚገናኝ አረጋግጧል፡፡ ከፍተኛ የሞት መጠን ከተመዘገበባቸው ህንድ በ103,587 ቀዳሚ ስትሆን ቻይና እና ኢንዶኔዢያ በሁለተኛ እና ሦስተኛነት እንደሚከተሉም ነው ድረ ገጹ ያስነበበው፡፡

በመጨረሻም የኘላስቲክ ምርት እና ኬሚካሉን ከመጠቀም መግታት እንዲቻል ዓለም አቀፍ አስገዳጅ ህግ ማውጣት ተገቢ መሆኑ ነው የተሰመረበት፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here