ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
70

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በሀገር ውስጥ ገበያ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ካለቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የጽህፈት የጽዳት ፣ኤሌለክትሮኒክስ  ፣የኤሌክትሪክ የፀረ-ሰብል ተባይ ኬሚካል ሞተር ሳይክል ጎማ ከነካላማዳሪዉ የብስክሌት ጎማ እና የአካባቢ ተፅእኖ ግምገማ ጥናት ዉጤት የአገልግሎት ግዥ ለመግዛት እና የተለያዩ ለዘር የማይሆኑ ሰብሎች ብጣሪዎች ፣ያገለገለ ጆንያዎችን እና ያገለገሉ እቃዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ፣ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት /ቲን/ ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርፕራይዙ ዋና መስሪያ ቤት ባሕር ዳር ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይዘጋል ፣በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሸጋገራል፡፡
  6. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  7. የተለያዩ ንፁህ ዘሮችና የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸዉ፡፡
  8. ያገለገሉ ጆንያዎች ብጣሪን በተመለከተ ንግድ ፈቃድ እንዲያቀርብ አይገደድም፡፡
  9. ግዥዉን በተመለከተ ባሕር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዘን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሌሎች ሰብሎችን በተመለከተ ባሕር ዳር ፣ኮምቦልቻ ፣እንጅባራ እንዲሁም ብር ሸለቆ የሚገኙ ሲሆን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ይመልከቱ፡፡
  10. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ኢንተርፕራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15 ወይም 09 18 01 69 35 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here