በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ሁለ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ የ2017 ዓ.ም አዲስ ምርት ነጭ በቆሎ በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሎት 1 ብዛት 5000 ኩ/ል ፣ሎት 2 ብዛት 5000 ኩ/ል እንዲሁም ሎት 3 ብዛት 5000 ኩ/ል የሚጫረቱ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፍ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መስሪያ ቤት ሂሳብ ክፍል እስከ 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጄው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
- የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- የማንሻ ጊዜ ለ5000 ኩ/ል 15 ተከታታይ ቀናት በጥቅል ከሆነ 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለበት፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
- የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ 04 ቀበሌ ከሚገኘው መጋዝን ይሆናል፡፡
- .ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ