የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ቡድን ለቢቡኝ ወረዳ እንስሳት ዓሳ ሃብት ጽ/ቤት የእንስሳት መድሐኒት በ2017 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ ለመጫረት የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአዲሱ አዋጅ መሠረት የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻዉ በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የግዥ ፈፃሚው እና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የጨረታ አሸናፊዉ የዉል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ/ በመሂ1 ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- የመድሀኒቱን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 200 /ሁለት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የመድሀኒት አቅርቦት ጠቅላላ ዋጋ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸዉን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግዥ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ከ11/09/2017 ዓ.ም እስከ 25/09/2017 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ/ን/አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በ16 ኛዉ ቀን በ26/09/2017 ዓ.ም 3፡00 ይታሸጋል በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ከፊት ለፈቱ መፈረም አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 00 47 /49 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት