ታክስ ከፋይ የሆኑት አቶ አብርሃም ብርሌው ደሳለኝ የሚፈለግባቸውን ታክስ ብር 11,267,714.62 (አስራ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አስራ አራት ብር ከ62/100) ስላልከፈሉ አድራሻው፡- ክልል- አማራ ፣ዞን -ባሕር ዳር ፣ክፍለ ከተማ -አጼ ቴዎድሮስ ፣ቀበሌ- 11 የቤት ቁጥር -A-191 ፣የቦታው ስፋት 3,000 ካሬ ሜትር ፣የቦታው ደረጃ፡- 1ኛ (አንደኛ) ፣ቦታው የሚሰጠው አገልግሎት፡- ለኢንዱስትሪ (ግንባታ እቃዎች ማምረቻ) ካርታ ቁጥር፡- 24742/2001 የቦታው አዋሳኝ በሰሜን ምሥራቅ 1.5 መንገድ ፣በሰሜን ምዕራብ ፣ጀሚላ አሊ ፣በደቡብ ምሥራቅ ዋይ ኤች ጂ ጠቅላላ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ዶ/ር ደግሰው አንዷለም የሆነውን የታክስ ባለዕዳውን ሀብቶች የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በአዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 41 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- የሀብቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት ብር 11,240,253.40 (አስራ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ አርባ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ ሶስት ብር 40/100)
- ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ከግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እስከ ከቀኑ 11:00 ነው፡፡
- ተጫራቾች ሀብቱን የሚገዙበትን ዋጋ በግልጽ በማስፈር በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው አድራሻው የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በማለት አስፍረው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቴሌቪዥን ጣቢያ ፣በጋዜጣ፣ እና በማስታወቂያ ቦርድ ከወጣበት ከግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 11:00 ድረስ ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ26/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ተዘግቶ በ27/09/2017 ዓ.ም በ4፡45 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያስያዘው ገንዘብ ከግዥው ዋጋ ታስቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈል ሀብቱን መረከብ አለበት፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ ለጨረታው ዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሁኖ የጨረታው አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
- ገቢዎች መምሪያ ስለ ሀብቶቹ አሻሻጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ሊሰርዝ ይችላል፡፡
- ስለሀብቱ አሻሻጥ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መመሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በአካል በመምጣት ማግኘት ይቻላል፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ