ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
146

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የግዥ ንብ/አስ/ቡድን ለእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት በ2017 በመደበኛ በጀት በጽ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ G+3 የቢሮ ግንባታ ለማስገንባት ስለፈለገ ተጫራቾችን ማንኛውንም የሚያስወጣ ማቴሪያልም ሆነ የስው ሀይል ተጫራቹ ራሱ ችሎ ማስራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ፡-

  1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ፣የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ ፣ምንም አይነት የግንባታ ሥራ ካልሰራ ላለመሰራቱ ከሚመለከተው መ/ቤት ደብዳቤ ማስጻፍ አለባቸው፡፡
  3. ማንኛውም ተቋራጭ GC/BC በደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆነ የታደሰ የግንባታ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ከጨረታው አሸናፊ ላይ 2 በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሃምሳ ሽህ ብር/ በሲፒኦ ፤በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ፤በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ሲኖርበት ጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ-1 ገቢ አድርገው ደረሰኙን ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ ከመሃንዲስ ግምት 25 በመቶ በታች ካልሆነ አጠቃላይ ከተወዳደሩበት 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ /በሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ሲኖርበት ከተዘጋጀው የመሃንዲስ ግምት ዋጋ አንፃር የተጋነነ ዝቅተኛ ከ25 በመቶ ዝቅ ብሎ ካቀረበ ለውል ማስከበሪያ 25 በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡
  6. በጨረታው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ወይም ተቋራጭ ዝርዝር የግንባታ ዋጋ /cost breakdown/ እና የግንባታ መርሃ ግብር /project work schedule/ እንዲሁም ባቀረበው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ /conformation letter/ አሸናፊነቱ በተገለጸ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህን ማድረግ ካልቻለ ከውድድር ውጭ ሆኖ ሁለተኛ የወጣው ተጫራች የሞላው ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ሆኖ ከተገኘ ሥራው ለዚሁ ተወዳዳሪ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
  7. ከተዘጋጀው የመሃንዲስ ግምት ዋጋ አንፃር የተጋነነ ዝቅተኛ ከ25 በመቶ ዝቅ ብሎ በመግባት አሸናፊ ሆነው የሚመረጡ የግንባታ ተቋራጮች ውል ይዘው ወደ ሥራ ሲገቡ የቅድሚያ ክፍያ እንደማይፈቀድ መታወቅ አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች ፖስታ ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያውን በመጨመር ቴክኒካል ዶክመንቱን ፣ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቹሀል፡፡ አሸናፊው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት እነ/ወ/ዐቃቢ ህግ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡
  9. ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጅምሮ የተሞላው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ግዜ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን ማስረጃ እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ እንዲታወቅ፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ ፋይናስ ቡድን ገ/ያዥ መግዛት አለባቹህ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን ማስረጃ እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቹሀል፡፡ የጨረታው መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ እንዲታወቅ፡፡
  12. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን 4፡00 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኝም የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ለተላለፈው ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን እሁድ ቅዳሜ እና የህዝብ በዓል ቢሆን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቀንና ስዓት ይከፈታል፡፡
  13. የወጣው የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ G+3 ቢሆንም ለጊዜው ግን የምናስገነባው G+1 መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡
  14. አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅትኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቾች አጠቃላይ የሥራ ዝርዝር እና ዲዛይን ከሰነዱ ጋር አብሮ የተያያዘ መሆኑን እንዲታወቅ፡፡ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቾች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡ ፓራፍ ቢያደረግም ውድቅ ይሆናል፡፡ በጨረታ ስነዱ በዋጋ መሙያው እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ማህተም ስምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡ ለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 01 00 /08 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here