ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

የሰ/ወሎ ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ ወልድያ ከሃምሌ 1/2017 ዓ.ም እሰከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሎት 1. ሰርገኛ ጤፍና የተከካ በቆሎ ፣ሎት 2 ፊኖ ነጭ የዳቦ ዱቄት እና ሎት 3. የባልትና ውጤቶች የሚያቀርቡ ነጋዴዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. በዚህው የሥራ መስክ ለመስራት የተመዘገቡ፡፡
  4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. አሸናፊው አካል በስማቸው የታተመ ደረሰኝ ያላቸው፡፡
  6. የሚሞላዉ ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጫራች /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
  7. ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ የሚቆይበት ጊዜ ከ18/09/17 እስከ 02/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ ብቻ ነዉ፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም /በሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ከ18/09/2017 እስከ 02/10/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከመ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ እስከ 03/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 3፡30 ድረስ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀዉ ሣጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ በዚሁ ቀን 03/10/17 ከረፋዱ 3፡30 ላይ ታሽጎ 4፡00 ላይ እራሣቸዉ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ያሸነፋበ\ትን እቃዎች በሙሉ በራሳቸዉ ወጭ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻ ማህተም ፊርማና ሌሎችን ማስረጃዎችን አሟልተዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  13. በጨረታዉ የሚቀርቡ ዕቃዎች በሙሉ ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
  14. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. የበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 331 12 40 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰ/ወሎ ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here