ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

ቁጥር ግጨ 08/2017

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በመደበኛ በጀት የቢሮ የጽዳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅት ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ፣የእቃው ግዥ መጠን ከ200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ ቢሮ ቁጥር 101 ወይም 102 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 250 (ሁለት መቶ አምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፓስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከመሙላቱ በፊት ቢሮው ድረስ በመምጣት የሚጸዱ ክፍሎችን በአካል ማየት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባሕር ዳር ከተማ በሚገኝው የአብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ላይ ይከፈታል፡፡
  4. ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን በ16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ብር 6,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፓስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን የጽዳት አገልግሎት አይነት አብክመ ገንዘብ ቢሮ ድረስ አገልግሎቱን ማቅረብ /መስጠት/ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡
  8. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን)፣መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ አብክመ ገንዘብ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 13 56 /058 220 08 39 በመደወል ማብራሪያ ማግኝት ይቻላል፡፡

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here