አሻሻጯ

0
60

በቻይና “ቼሪ” የተሰኘው ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ምርቶቹን ለማስታዋወቅ ሰው ሰራሽ ማሽን ወይም “ሮቦትን” ማሌዥያ በሚገኘው የሽያጭ ማእከሉ አገልግሎት ላይ ማዋሉን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ከሳምንት በፊት ለንባብ አብቅቶታል፡፡

የሰው ሰራሽ ሮቦቱ ንድፍ ፋና ወጊ እንደመሆኑ በማህበራዊ ድረ ገፆች የሚሰሙትን ፅንሰ ሀሳቦች መሰረት አድርጐ ከወጣቱ  ትውልድ  ደንበኞች ጋር ለመግባባት እና መስተጋብር መፍጠርን ታሳቢ አድርጐ ነው የተፈበረከው፡፡

አዲሷ “ምርኒን” የተሰኘችው ሰው ሰራሽ አሻሻጭ  የሸማቾችን መልእክቶች እና ትእዛዞች  መገንዘብ እንድትችል መልእክት ተቀባይ ዳሳሽ ወይም (ሴንሰር ) ተገጥሞላታል፡፡ ተፈጥሯዊ ቋንቋን በመረዳት  ውሳኔዎችን ለመውሰድ ወይም ለመስጠትም ዲኘሲክ (Deepseek)ን የቋንቋ መገንዘቢያ ስልት አድርጋ እንደምትገለገል ነው የተገለፀው፡፡

“ሞርኒን” አዲሷ አሻሻጭ ወይም ሽያጭ አከናዋኝ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2023 እ.አ.አ ለእይታ የበቃች ሲሆን በ2025 በማሌዥያ ኳላላምፑር ረዳት የሽያጭ አከናዋኝ ሆና መሰማራቷም ነው ለንባብ የበቃው፡፡

ሰው ሰራሽ  አሻሻጯ ለገዢ ደንበኞች ስለተሽከርካሪዋ ሙሉ መረጃ፣ ለሚቀርቡላት ጥያቄዎች መልስ ትሰጣለች፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here