ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ መድሂኒቶችን እና የህክምና መሳሪያዎችን ለማስገባት ባወጣው የኢምፖርት ፈቃድ ቁጥር 13132/MEMDICER/2024 መሰረት ሀገር ውስጥ ካሉ የህክምና መሳሪያ አምራቾች ፣አስመጭዎችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን የህክምና መሳሪያዎች መሸጫ ዋጋ ትራንስፖርትን በመጨመር አካተው ከድርጅቱ መስሪያ ቤት ባሕር ዳር ድረስ እንዲያቀርቡ ይፈልጋል፡፡ 1. Clinical Chemistry ብዛት 03 ፣2. BP Apparatus Digital ብዛት 10 ፣3. Salter Scale ብዛት 22 ፣4. Anesthesia Machine each ብዛት 02 እና 5. Patient Monitor each ብዛት 30 ስለዚህ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ዋጋ ሞልተው ሲያቀርቡ የህክምና መሳሪያዎች አስመጭ መሆናቸውን የሚገልጽ EFDA ሰርተፊኬት እና ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር ፣የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በ05/10/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ላይ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ባ/ዳር ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒካል ፕሮፖዛል የዋጋ ማቅረቢያ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ 2 በመቶ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፣አቅራቢው ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ተገልፆ በግዴታው ወይም በውሉ መሰረት ካልፈፀመ ያስያዘው 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያው የማይመለስ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የጨረታው ውጤት የሚገለፀው በደብዳቤ ወይም በኢሜል ይሆናል፡፡
- ተወዳዳሪዎች አሸናፊ መሆናቸው በፁሁፍ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ ያሸነፉበትን የህክምና እቃዎች ለድርጅቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚያቀርቧቸውን እቃዎች ድርጅቱ ዘርዝሮ ባስቀመጣቸው ስፔስፊኬሽን መሰረት ብቻ ይሆናል ፣ይህም የሚገዙት ሰነድ ላይ ተያይዞ ይገኛል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃዎቹን ካቀረበ በኋላ የማሽኑን አጠቃቀም ስልጠና መስጠት ይኖርበታል፡፡
- የሚፈለጉ እቃዎች ስፔስፊኬሽን በተመለከተ ከድርጅቱ መስሪያ ቤት በመምጣት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሰነድ መግዣ ብር 3000 /ሶስት ሽህ ብር/ በመያዝ መግዛት ይቻላል፡፡
- ሰነዱን የሚያቀርቡበት መንገድ በአካል ወይም በፖስታ 1555 ስልክ ቁጥር 058 830 45 50/ 058 320 70 68 አድራሻ ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ኖክ አካባቢ ሪየስ ኢንጅነሪንግ 2ኛ ፎቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻችን medxdiagnostics2013@gmail.com መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ