በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የአዲስ አለም ሆስፒታል የአገልግሎት ሎት 1. ኪችን ካብኔት፣ ሎት 2. ሸልፍ፣ ሎት 3. የማስታወቂያ ቦርድ ረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
- ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- 4 ቱም በሎት የወጡ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደሩ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሰፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 3፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን 10 በመቶ የውል ማስያዣ ያስይዛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሀሳቡን በታሸገ ፖስታ በአዲስ አለም ሆስፒታል ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582181034 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- በሎት ድምር ዋጋ የሚታየው የውድድር ጨረታ ለመ/ቤቱ የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ በተናጠል ዋጋ አሸናፊው ሊለይ ይችላል፡፡
ሕር ዳር የአዲስ አለም ሆስፒታል