ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
137

የጨረታ ቁጥር፡- 03/2017

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት በአብክመ ጤና ቢሮ ከጣሊያን መንግስት ባገኘው የበጀት ድጋፍ ለደጀን የመጀ/ደ/ሆስፒታል መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ ንፅህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ GC-9/WWC-6 እና በላይ ጥልቅ ጉድጓድ ንፅህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ግንባታ ሥራ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋዩ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠኑ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ ሰነድ በመግዛት ደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 85 መዉስድ ይቻላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚሰራውን መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ ንፅህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ግንባታ ሥራ በተሰጠዉ ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሙላት አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ ንፅህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ግንባታ ሥራ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ ፣ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያዉ ላይ በመፈረም ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ በ22ኛዉ ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡30 ድረስ በሆስፒታሉ ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 85 በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ ጨረታዉ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታዉን ይከፍታል፡፡ የጨረታዉ ሰነድ መግዛት የሚቻለዉ እስከ 30ኛዉ ቀን 11፡30 ድረስ ብቻ ነዉ፡፡
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. መ/ቤቱ ጨረታዉን በሎት የሚያወዳድር ሲሆን የተዘረዘሩ ስራዎችን ሁሉንም ሳይሞሉ መተው ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  11. ተጫራቾች ያሸነፉትን መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ ንፅህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ግንባታ ሥራ ደጀን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እጥር ግቢ ውስጥ በተመረጠው ቦታ መስራት አለባቸው፡፡
  12. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 ሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 5 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርቦ ዉል መያዝ አለበት፡፡
  13. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ተጫራቾች 10 በመቶ ፐርፎርማንስ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  15. የክፍያ ሁኔታ ተቆጣጣሪ መሀንዲሱ ባስቀመጠው ሥራ ዝርዝር በተሰራው ሥራ ልክ የሚከፈል ሆኖ ቅድሚያ ክፍያ አይሰጥም፡፡
  16. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 85 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 04 56 00 11 /058 776 13 18/ መደወል ይቻላሉ፡፡

የደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here