ጉዳት የለሹ ማስታገሻ

0
56

የዱክ ዩኒቨርሲቲ በአሜሪካ ሰሜን ካሮላይና ተመራማሪዎች ከባድ ቀዶ ህክምና፣ በአጥንት መሰንጠቅ፣ በነርቭ ጉዳት የመሳሰሉትን በማከም ሂደት የጎንዬሽ ጉዳት የማያስከትል የህመም ማስታገሻ ማግኘታቸውን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ  ለንባብ አብቅቶታል፡፡

በሙከራ የተገኘው የጐንዮሽ ጉዳት የማያስከትለው (SBI-810) በሚል የተሰየመው ውህድ የህመም ማስታገሻ በጀርባ አካርካሪ እና በደምስር መልእክት ተቀባይ ላይ የሚያነጣጥር ነው፡፡

 

አዲሱ የህመም ማስታገሻ (SBI-810) ከነባሩ ወይም (opioids) የሚለየው የተለየ አካልን ነጥሎ የሚሰጥ መሆኑ ነው። ነባሩ (opioids) ግን ሁሉንም አካል ሳይለይ ያጥለቀልቃል-እንደ ተመራማሪዎቹ አገላለጽ።

በተጨማሪም (opioids) ከህመም ማስታገሻነቱ ባሻገር ይዘቱ ህሙማኑን ሱስ ሊያስይዝ ስለሚችል ከሌሎች ጋር ተዋህዶ በአነስተኛ መጠን ለጉዳት ሳይዳርግ መከወን ያስችላል ነው የተባለው፡፡

 

ምርምሩን የመሩት ዶክተር ሩ ሮንግጂ አዲሱ ውህድ ሱስ የማያስይዝ የህመም ማስታገሻ ለሰዎች ከመሰጠቱ በፊት ለሙከራ በተመረጡ እንስሳት ላይ ተሞክሮ ተረጋግጧል ነው ያሉት፡፡

አዲሱን ውህድ ማስታገሻ ፈጥኖ አገልግሎት ላይ ለማዋል  ዝግጅቱ በመፋጠን ላይ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር በመጨመሩ እንዲሁም በ(opioids)የሚሞቱት ቁጥር በማሻቀቡ ነው፡፡

 

በውህዱ ህመም ማስታገሻነት የአጥንት መሰንጠቅ እና የነርቭ ጉዳት የመሳሰሉትን በቀዶ ህክምና ለማከም የተሻለ ተስፋ ሰጪ ማስታገሻ መሆኑን ነው ያሰመሩበት- የምርምሩ መሪ ዶክተር ሩ ሮንግጂ፡፡ ውህዱ ቀደም ብሎ ይታዩ የነበሩ የማስታወስ ዓቅም መንሳት፤ ሱስ ማስያዝ የመሳሰሉትን በሚፈለገው አካል ላይ ብቻ አነጣጣሮ በመስጠት የጐንዮሽ ጉዳቶችን ማስቀረት የሚችል መሆኑን  በተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here