በቁርጥራጭ ኘላስቲክ የተሞሉ አእዋፍት

0
56

አውስትራሊያን በስተምሥራቅ በሚያዋስናት ባሕር  “ሎርድ ሃው” በተሰኘች ደሴት በሚገኙ  ወፎች በአማካይ በእያንዳንዳቸው ከክብደታቸው አንድ አምስተኛ የሚመዝን ቁርጥራጭ ኘላስቲክ መገኘቱን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ  አስነብቧል፡፡

በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ በተፈጠረችው “ሎርድ ሃው” ደሴት 500 የሚጠጉ ሰዎች እንዲሁም በከበባት የውኃ አካል ላይ ደግሞ 40 ሺህ ክንፈ ረዣዠም የባህር ዓእዋፍ ይኖራሉ ተብሎ ይገምታል፡፡ የደሴቷ መገኛ ከብክለት የራቀ ቢመስልም ለዓመታት ምርምር ያደረጉ ምሁራን ግን አሳሳቢ ሁነት ማግኘታቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

 

ቀደም ብሎ በ2024 እ.አ.አ ተመራማዎች ባካሄዱት ምርምር በአንድ ወፍ ሆድ እቃ የተገኘው ከፍተኛ የኘላስቲክ ቁርጥራጭ ብዛት 403 ብቻ ነበር፡፡ ተመራማዎቹ በ2025 እ.አ.አ በተከታታይ ባደረጉት ፍተሻ ደግሞ 778 የኘላስቲክ ቁርጥራጭ በአንድ ወፍ ሆድ እቃ ማግኘት ችለዋል፡፡

 

ግኝቱን ተከትሎ ተመራማሪዎች አስጊ እና አሳሳቢነቱ በእጅጉ የጐላ መሆኑን ነው ያሰመሩበት፡፡ ከባህሩ ላይ የሚንሳፈፍ ቁርጥራጭ ኘላስቲክን እንደ ዓሳ በመያዝ ከራሳቸው አልፈው በጐጆቸው ወስደው መብረር ላልጀመሩ ጫጩቶቻቸውም መግበዋቸዋል፤ በግኝቱ እንዳመላከተው፡፡   በጫጩቶቹ ሆድ እቃ  ብዛት ያለው የኘላስቲክ ቁርጥራጭ መገኘቱ ሁሉንም ወገን በእጅጉ ሊያሳስብ እንደሚገባ ነው ተመራማሪዎቹ በአፅንኦት ያሰመሩበት፡፡

ተመራማሪዎቹ ትኩረት ካደረጉበት “የሎርድ ሃው “ደሴት ባሻገርም ሁነቱ በሌሎች የውኅ አካላት ላይ ተመሳሳይ መሆኑን ገልፀዋል።

የባህር ላይ ዓእዋፍ የሚበሉት የኘላስቲክ መጠንም ሆነ በዚህ ምክንያት ለሞት የሚዳረጉት  ቁጥራቸው በእጅጉ እየጨመረ መሆኑን ነው ተመራማሪዎቹ ያሳሰቡት።

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here