ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
57

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም  ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች  መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር  /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ የሙያ እና የንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፡፡
  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዪጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፤ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ካደረጋቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባህር ዳር ከተማ በሚገኘዉ የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቀው የሚሳተፍ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ፣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከፍሎ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይቻላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ ፣ የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ  ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 12 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  1. የጨረታ ሳጥኑ በአስረኛዉ የሥራ ቀን፤ ከቀኑ በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ወይም እለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ከቀኑ በ8፡30 በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
  2. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0583208415 ወይም 0918016935 ፋክስ 0582266002 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here