የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
52

የክምር ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በሊዝ መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 7 ለድርጅት 2 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 9 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽት 11፡30 በሥራ ሰዓት ከተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ ፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መሪ ማ/ቤት አዳራሽ ይሆናል፡፡
  5. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ቦታውን በመስክ ለመጎብኘት ከፈለጉ ከክምር ድንጋይ ማዘጋጃ ቤት ድረስ በመምጣት ከጨረታ ኮሚቴው ጋር መጎብኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለድርጅት 15 በመቶ ለመኖሪያ 10 በመቶ ህጋዊ በሆነ ባንክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ ወይም በስ.ቁ 09 18 71 44 11 ደውለው ማግኘት ይችላሉ

የክምር ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here