በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጉና በጌምድር ወረዳ የክምር ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት ለዲች ሥራ የሚውል ስሚንቶ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 - የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ቁጥር ያላቸው፡፡
 - ያቀረቡት ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 - ግብር የከፈሉበት ክሊራስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 - ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ /በሲፒኦ/ በባንክ በክ/ድንጋይ መሪ ማ/ቤት ስም ያስይዛሉ፡፡
 - ከ1-5 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 - ጨረታው ተጫረቾች /ህጋዊ ወኪሎቻው/ በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 12 በ15 ተኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
 - የስሚንቶ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
 - ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን ሥርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቹን ስም ፊርማ ማህተም እና ጨረታ ያወጣውን መ/ቤት ስምና አድራሻ በመግለጽ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ክ/ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት ባዘጋጀው ሳጥን ያስገባሉ፡፡
 - ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
 - የአንዱን ኩንታል ዋጋ እና የጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው፡፡ የ 1 ሰነድ ዋጋ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ነው፡፡
 - አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፅበት 5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ክ/ድንጋይ መሪ ማ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
 - ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 
ማሳሰቢያ፡- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ 09 18 71 44 11 መደወል ይቻላል፡፡
የክምር ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት

