ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
87

በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው የአዊ ልማት ማህበር ኤሌክትሮኒክስ፣ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፍሮ እና ፍራሽ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግዥው ከ200,000/ከሁለት መቶ ሺህ/ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ጠቅላላ ዋጋውን (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላት በታሸገ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በመለያየትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ተኛው ቀን 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊው ድርጅት 10 በመቶ ውል ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  9. የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስላቸው አሸናፊው ውል ከያዘ በኋላ ነው፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582270362 / 0582271188 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአዊ ልማት ማህበር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here