በአፈ/ከሳሽ ጌች ግሮሰሪ እቁብ ማህበር ሰብሳቢ አለኸኝ ልየው እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ወ/ሮ በላይነሽ አለነ 3ቱ ራሳቸው መካከል ስላለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 05 በሰሜን ዳኛው እምሬ፣ በደቡብ እና በምእራብ መንገድ፣ በምስራቅ ጋሻው ደሳለው የሚያዋስነው እና በአፈ ተከሳሽ በወ/ሮ በላይነሽ አለነ ባለቤት በአቶ መልካሙ አሸነፍ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት የመነሻ ዋጋው 1,920,000 /አንድ ሚሊዩን ዘጠኝ መቶ ሀያ ሽህ /ብር በጫረታ ይሸጣል፡፡ ስለሆነም ከሰኔ 2/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 2/2017 ዓ.ም ለ30 ቀን በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ ሐምሌ 3/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ጫረታው ይካሄዳል፡፡ ውጤቱም ሐምሌ 3/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 የሚገለጽ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት