በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው የአዊ ልማት ማህበር ያስገነባውን ህንፃ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ክፍሎችን ማለትም ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለቢሮዎች እና ፔንሲዎን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር00 /ሁለት መቶ/ በመግዛት ጠቅላላ ዋጋውን (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላት በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በመለያየትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ማስታወቂያው ጋዜጣ በወጣበት በ16ተኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት 10በመቶ ውል ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስላቸው አሸናፊው ውል ከያዘ በኋላ ነው፡፡
- ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582270362/0582271188 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዊ ልማት ማህበር