ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ለ2018 በጀት አመት አመታዊ የተሸከርካሪ ሙሉ የመድን ዋስትና ኢንሹራንስ ሽፋን /የሶስተኛ ወገን/ ግዥ በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የአገልግሎቱ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ላይ የሚገለጸውን ዋጋ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300/ ሶስት መቶ /ብር ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 128 ማግኘት ይችላሉ ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን በሎጀ/ ፋይ/አስ/ ም/ዘርፍ ወይም ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እሰከ ሰኔ16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ተዘግቶ በቀን 17/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር 103/46 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582201453 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here