በአፈ/ተከሳሽ መጣልኝ ጌትነት እና በአፈ/ተከሳሽ ጥላነሽ ባዜ መካከል ስላለው አፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በዘጌ 01 ቀበሌ ገዳም ሰፈር በአፈ/ተከሳሽ ወ/ሮ ጥላነሽ ባዜ ወንዴ ስም ተመዝግቦ የሚገኝውን በምሥራቅ በቁጥር 904 ፣በምዕራብ በቁጥር 900 በሰሜን በቁጥር 901 እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል ተዋስኖ የሚገኘውን 200 ካ.ሜትር ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 811,542.4 (ስምንት መቶ አስራ አንድ ሺህ አምስት መቶ አርባ ሁለት ብር ከ40 ሳንቲም) ሀምሌ 12 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ የፍ/ቤቱ ሐራጅ ባይም ጨረታው በሚካሄድበት በዘጌ 01 ቀበሌ ገዳም ሰፈር ንብረቱ በሚገኝበት በመገኘት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱና በቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፡- በዕለቱ ጨረታውን ያሸነፈ ያሸነፈበትን 1/4 ኛውን በሞ/85 ጨረታው እንደተጠናቀቀ የሚያዝ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከ/ፍ/ቤት