ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
113

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቀስ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና የአደጋ ምላሽ ሥራዎች ዙሪያ ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ለሥራ ሲጠቀምባቸው የነበሩ በማህበሩ ዋናዉ መ/ቤት ባህርዳር እና አዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት የሚገኙ 9 የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. መግዛት የሚፈልግ ማንኛዉም ግለሰብ/ድርጅት መግዛት ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በአማራ ልማት ማህበር ዋናው መ/ቤት ባህርዳር ቢሮ ቁጥር 108 መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፣
  4. ተጫራቾች የሚሸጡትን የተሸከርካሪዎች ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሠነዱ ላይ በማየት በማህበሩ ዋናዉ መ/ቤት እና አዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት በአካል በማየት ዋጋዉን በዋጋ መሙያ ቅጽ መሠረት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ20 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/  ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  5. ጨረታዉ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ስዓት ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ስዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራች ድርጅቶች የሚያቀርቡት የተሸከርካሪ ዋጋ ከመነሻ ዋጋ ማነስ የለበትም፡፡ ከመነሻ ዋጋ በታች ዋጋ የሞሉ ተጫራቾች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ከ5 ተከታታይ ቀናት በኋላ የሚቆጠር በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ዉል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማህበሩ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583207360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ)

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here