በአፈ/ከሳሽ አዝመራው ሙላት እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ጌትነት የኔ አባት 3ቱ ራሳቸው መካከል ባለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በእን/ከተ/አስ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ፣በምዕራብ እና በሰሜን ክፍት ቦታ እንዲሁም በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው በወ/ሮ ውዴ ጌታነህ ጥሩነህ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት የፍርድ ባለ ዕዳ ስለሆኑ በጨረታ ይሸጣል፡፡ የመጫረቻ መነሻ ዋጋ 683,824 /ስድስት መቶ ሰማንያ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ አራት ብር/ ሰኔ 09 ቀን 2017 እስከ ሀምሌ 09/2017 ዓ.ም በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ይቆይና ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም 2፡30 እስከ 6፡00 ጨረታው የሚካሄድ መሆኑን አውቃችሁ ቦታው ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት