ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
111

የጨረታ ቁጥር አብክመ ገቢ/የሚ/ተሸ/01/10/2017

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በክልል ቢሮዎች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በዞኖችና በወረዳዎች የሚገኙ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ማለትም፡-(መኪናዎች ፣ ትራክተሮች ባጃጅ እና ሞተር ሳይክሎች ) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሠነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ/ ብር ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ከ12/10/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/11/2017 ዓ/ም 11፡00 ድረስ የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ተሽከርካሪ የሞሉትን የጠቅላላ ድምር ዋጋዉን 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም 60 ቀን ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በአንድ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በአብክመ ገንዘብ ቢሮ ስም በማሰራት በአንድ ፖስታ ብቻ በማሸግ በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የተሽከርካሪ ዋጋ የሞላበትን ገጽ ብቻ ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ12/10/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/11/2017 ዓ/ም 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 በ02/11/2017 ዓ/ም 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 02/11/2017 ዓ/ም 4:30 ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ተሽከርካሪዎችን በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በተገለፀዉ ቦታ ከ12/10/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/11/2017 ዓ/ም 11:00 ድረስ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ በመሄድ  በአካል ማየት ይችላሉ፡፡ ርክክብ የሚፈጸመዉም በጨረታ ሠነዱ ላይ በተቀመጠዉ ቦታ ነዉ፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነዉ በተናጠል በተሰጣቸው የሠሌዳ ቁጥር ወይም መለያ ቁጥር መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች በፖስታቸዉ ላይ ስም ከነአያት፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸዉ፡፡
  10. ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-220-45-07 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 አድራሻ፡- ባህር ዳር ከተማ ከድሮዉ ዲፖ አካባቢ ይገኛል፡፡

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here