ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
107

የዳንግላ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የ2015 እና የ2016 በጀት ዓመት ከሀምሌ 01-11-2014 እስከ 30-10-2016 ዓ.ም የ2ዓመት ሂሣብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች በግልፅ ጨረታ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር ከፍለው የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሱ፡፡
  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ተቋሞቹ የሚሰጡ ከሆነ)፡፡
  4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በዳንግላ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
  5. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ፣ ወይም በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር ከፍለዉ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ ፣የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ማሲያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል::
  7. የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን በ3፡00 ስዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ3፡30 በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 4 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎ በስልክ ቁጥር 0918710156 ወይም 0918710153 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡

         የዳንግላ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here