ኬንያን በመስህቦች

0
71

የኬንያ ሪፐብሊክ በምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2024 የሕዝብ ቁጥሯ ከ52 ሚሊዮን በላይ ነበር፡፡ ኬንያ በሕዝብ ብዛት በዓለም 27ኛዋ፣ በአፍሪካ ደግሞ ሰባተኛዋ ሀገር ናት። የኬንያ ትልቁ እና ዋና ከተማዋ ናይሮቢ ነው። ሁለተኛው አንጋፋና ትልቁ ከተማዋ  ሞምባሳ ይባላል። በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች መካከል ደግሞ ኪሱሙ፣ ናኩሩ እና ኤልዶሬት ይገኙበታል። የኬንያ ሪፐብሊክ በምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በሰሜን ከኢትዮጵያ፣ በሰሜን-ምስራቅ ከሶማሊያ፣ በደቡብ ከታንዛኒያ፣ በምስራቅ ከዩጋንዳ፣ በሰሜን-ምዕራብ ከደቡብ ሱዳን፣ በደቡብ-ምስራቅ ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር ድንበር ትጋራለች።

አውሮፓውያን አካባቢውን ማሰስ የጀመሩት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲሆን የብሪታንያ መንግሥት የምሥራቅ አፍሪካ ፕሮቴክቶሬትን (ጠባቂ) በ1895 እ.አ.አ. አቋቁሟል። ይህ ፕሮቴክቶሬት በ1920 እ.አ.አ. የኬንያ ግዛት ተብሎ ተሰይሟል። ነፃ የኬንያ ሪፐብሊክ በ1963 እ.አ.አ. ታውጇል።

የኬንያ ስም የመጣው በአፍሪካ በከፍታ ሁለተኛ ከሆነው ኬንያ ተራራ ነው። በዚሁ ተራራ ዙሪያ የሚኖሩት ነገዶች ስሙን «ኪኛ» (በካምባኛ)፣ «ኪሪማራ» (በአመሩኛ)፣ «ኪሬኛ» (በኤምቡኛ)፣ «ኪሪኛጋ» (በኪኩዩ)፣ ወይም «ኬሪ» (በመዓሳይኛ) ይሉታል። የነዚህ ስሞች ሁሉ ትርጉሞች «ቡራቡሬ» ሲሆኑ ይህም ደግሞ «ሰጎን» ማለት ነው፤ አመዳይ ያለበት የተራራው ጫፍ ለተመልካች ቡራቡሬ ወንድ ሰጎንን ያሳስባልና።

ኬንያ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት አጠቃላይ ሀገራዊ ምርቷ ወደ 400 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነው፡፡ የህዝቧ የነብስ ወከፍ ገቢም ሰባት ሺህ ዶላር አካባቢ ነው፡፡ ይህም በአፍሪካ የተሻለ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት ቀዳሚም ባይሆን መካከለኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል፡፡ በአፍሪካ በቴክነኖሎጂው ዘርፍ የተሻለ እንቅስቃሴ ካላቸው ሀገራት ትመደባለች፡፡ የተለያዩ ዘርፎችንም ለውጪ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረጓም ይነገራል፡፡ ሆኖም አብዛኛው ኢኮኖሚዋ በውጪ ባለሀብቶች እንደሚዘወርም የሚጠቅሱ አልጠፉም፡፡

ቱሪዝም በኬንያ ኢኮኖሚ ስድስት በመቶውን ያበረክታል። ዋነኞቹ የቱሪስት መስህቦች 60  ብሔራዊ ፓርኮች እና የጨዋታ መዝናኛዎች (ሳፋሪዎች) ናቸው። ታሪካዊ መስጊዶች እና በቅኝ ግዛት ዘመን በሞምባሳ፣ማሊንዲ እና ላሙ የተሠሩ ምሽጎችም የጉብኝት መዳረሻዎች ናቸው፡፡

የአፍሪካ “ትልቅ አምስት” የዱር እንስሳት ማለትም አንበሳ፣ ነብር፣ ጎሽ፣ አውራሪስ እና ዝሆን በኬንያ እና በተለይም በማሳይ ማራ ይገኛሉ። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሌሎች የዱር እንስሳት፣ ተሳቢ እንስሳት እና አእዋፍ በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ብሔራዊ ፓርኮች እና ዱሮች ውስጥ ይገኛሉ። ዓመታዊ የእንስሳት ፍልሰት ከሰኔ እስከ መስከረም ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንስሳት ወደ ኬንያ ይፈልሳሉ፡፡

የማዕከላዊ የኬንያ ወረዳ፣ ልክ እንደ ስሙ እንደሚያመለክተው የኬንያ ማዕከላዊ ክፍል ነው፡፡ በቀድሞው ኋይት ሃይላንድስ (ነጫጭ ደሴቶች) ይባል ነበር፣ በአሁኑ ጊዜ የኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢን ጨምሮ ይሸፍናል። የኬንያ ማእከላዊ ወረዳ ተራራማ እና ገደላማ እንዲሁም ቁልቁለታማ በመሆኑ ለጀብደኛ ጎብኚዎች አመቺ መድረሻ ነው። በማዕከላዊ የኬንያ ወረዳ በብዛት የሚጎበኙ መዳረሻዎች የኬንያ ተራራ ብሔራዊ ፓርክ፣ ሎንጎኖት ተራራ ብሔራዊ ፓርክ እና አበርዳሬ ብሔራዊ ፓርክን ያካትታሉ።

ኬንያ ውስጥ ጎብኝዎች  ከሚጎበኟቸው ሰባት ወረዳዎች መካከል የደቡብ ሪፍት ወረዳ ሌላው ነው። የኬንያ ሳፋሪስ ዓመቱን በሙሉ  ይጎበኛል። የደቡብ ስምጥ ወረዳ በኬንያ ውስጥ በጣም የሚፈለጉትን እና ተወዳጅ መስህቦችን እና መዳረሻዎችን የሚያጠቃልል ነው፡፡ የሚያማልሉ ትእይንቶችን እና በሺዎች የሚቆጠሩ የዱር እንስሳት ዝርያዎችን መመልከት ያስችላል። ተጓዦች ከአስደናቂ እና የመጨረሻ የኬንያ ሳፋሪ ተሞክሮዎች በኋላ በደቡብ ሪፍት ወረዳ የሙቅ አየር ፊኛ ጉዞ (ባሎን)፣ የጫካ ቁርስ፣ የጫካ እራት፣ የፀሐይ መጥለቅ እይታ፣ የፈረስ ግልቢያ፣ የእግር ጉዞ እና ሌሎች አስዳናቂ ነገሮችን መጎብኘት ይቻላል። የደቡብ ወረዳ የሄል በር ብሔራዊ ፓርክ፣ የናኩሩ ሐይቅ ብሔራዊ ፓርክ፣ ማሳይ ማራ ብሔራዊ ሪዘርቭ እና የማራ ትሪያንግልን ያጠቃልላል።

የምስራቁ ወረዳ ከናይሮቢ ወጣ ብሎ ነው የሚገኘው። የምስራቃዊው ወረዳ በሚያስደንቅ ሁኔታ በበለፀገው የኬንያ ባህል ታዋቂ ነው፤ የተለያዩ እንስሳትን እና በጣም የሚያምሩ ሎጆችን እና ካምፖችን ይዟል፡፡ የዱር እንስሳት አድናቂዎች በጣም ያዘወትሩታል። የኬንያ ምስራቃዊ ወረዳ የሳምቡሩ ጨዋታ ማዕከል፣ ኦል ዶይንዮ ሳቡክ ብሔራዊ ፓርክ፣ ሜሩ ብሔራዊ ፓርክ፣ ቡፋሎ ስፕሪንግስ ብሄራዊ ሪዘርቭ እና ምዌ ብሔራዊ የጥበቃ ጣቢያን ያካትታል።

በኬንያ ከሚገኙ ሰባቱ የቱሪዝም ወረዳዎች አንዱ የሆነው የሰሜን ሪፍት ወረዳ ቱሪስቶች በስፋት ከሚጎበኟቸው ውስጥ ነው። የሰሜን ስምጥ ወረዳ እጅግ አስደናቂ የሆነ ወጣ ገባ መሬት እና አስደናቂ መልክዓ ምድሮችን ያቀፈ ነው፡፡ እንዲሁም የሚማርክ ስምጥ ሸለቆ እና በርካታ የኬንያ የዱር እንስሳት ፓርኮች እና ማደሪያ ስፍራዎች አሉት። የላይኪፒያ ብሔራዊ ጥበቃ (የእንስሳት እና እጽዋት) ጣቢያ፣ ደቡብ ቱርካና ብሔራዊ ጥበቃ ጣቢያ፣ ማርሳቢት ብሔራዊ ጥበቃ ጣቢያ እና ናሳሎት ብሔራዊ ጥበቃ ጣቢያ የማይረሱ ተሞክሮዎችን የሚያሳልፉባቸው ናቸው፡፡

የኬንያ ደቡባዊ ወረዳ የሆነው የጻቮ ብሔራዊ ፓርክ የቀይ ዝሆኖች መኖሪያ ነው፤ ለማይረሱ የኬንያ ሳፋሪ ጉብኝቶች አስደናቂ ቦታ ነው። በዚሁ አካባቢ ተጓዦች የባህር ዳርቻዎች ላይ መዝናናት ይችላሉ።

(ቢኒያም መስፍን)

በኲር የሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here