ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
95

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የሚገኘው የመገናኛ ሁለ/የገበ/ኅ/ሥራ ማህበራት ዬኒየን ኃ/የተወሰነ የሰራተኛ ደንብ ልብስ 1ኛ ሎት /ምድብ አንድ/ የተለያየ አይነት ልብስና ቆብ እንዲሁም 2ኛ ሎት /ምድብ ሁለት/ ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጥቅል ዋጋ መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ሁለት በመቶ በባንክ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ዋስትና አስይዘው ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡ ከዩኒየኑ በጥሬ ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ የሚያሲዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆነ) አቅርቦቶች ካልሆነ በስተቀር በግዥው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል ሎት የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዬኒየኑ የጨረታ ሰነዱን መግዛት አለባቸው፡፡ እንዲሁም የተጫራቾች መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ይሰጣል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የሥራ ዝርዝር አገልግሎት ሥርዝ ድልዝ ሳይኖራው የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋውን ሞልተው በፖስታ አሽገው ከዬኒያኑ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በወቅቱ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊው ተወዳዳሪ የሚለየው በሎት ምድብ ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሆኑ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም የደንብ ልብስ አይነቶች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ተጫራቹ መሙላት አለበት፡፡
  7. ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10 ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን ከላይ በተገለጸው ተማሳሳይ ስዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች ተወዳድሮ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ /በሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ አስይዞ በ5 ቀን ውስጥ ከዬኒየኑ ቀርቦ ውል መውስድ አለበት፡፡
  9. አሸናፊው ተወዳዳሪ ያሸነፈበትን የደንብ ልብስ ደብረ ታቦር ከተማ ከዩኒየኑ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጭ አጓጓዞ ማቅረብ አለበት፡፡
  10. ዩኒየኑ ያወጣውን ጨረታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  11. ቅዳሜ ከስዓት በፊት እስከ 6፡30 ድረስ የዩኒየኑ የሥራ ቀን ነው፡፡
  12. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 እና 058 141 99 27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ ፡-ደ/ታቦር ከተማ ጸደይ ዋናው ባንክ አንደኛ ፎቅ ነው፡፡

መገናኛ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተወሰነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here