ሜዴክስ ዲያግኖስቲክ መድሀኒቶችን እና የህክምና መሳሪያዎችን ለማስገባት ባወጣው የኢምፖርት ፈቃድ ቁጥር 13132/MEMDICER/2024 መሰረት ሀገር ውስጥ ካሉ የህክምና መሳሪያዎችን አምራቾች እና አስመጭዎች በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን የህክምና መሳሪያዎች መሸጫ ዋጋ ትራንስፖርትን በመጨመር ከድርጀቱ መስሪያ ቤት ባህርዳር ድረስ እንዲያቀርቡ ይፈልጋል:: ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሚሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- Hematology Analyzer ብዛት 3 የተለያዩ መመርመሪያ ቴስቶች ::
- ዋጋ ሞልተው ሲያቀርቡ የህክምና መሳሪያ አስመጭ መሆናቸው የሚገልፅ EFDA ሰርቲፊኬት እና ፈቃድ የላቸው መሆን አለባቸው ::
- በዘርፉ የታደስ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር ማያያዝ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል::
- የጨረታው ሰነድ 01/11/17 ከጠዋቱ 4̃:00 ላይ ተወካዮች ባሉበት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል::
- የጨረታው ውጤት የሚገለፀው በደብዳቤ ወይም በኢሜል ይሆናል ::
- ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
- የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ 2በመቶ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል :: አቅራቢው ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ተገልፆ በግዴታው ወይም በውሉ መሰረት ካልፈፀመ ያስያዘው 2 በመቶ የማይመለስ ይሆናል::
- የሚያቀርባቸው እቃዎች ድርጅቱ ባቀረባቸው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ብቻ ይሆናል::
- አሸናፊው ድርጅት እቃዎቹን ካቀረበ በኋላ የማሽኑን አጠቃቀም ስልጠና መስጠት ማስጀመሪያ ሪኤጀንት ማቅረብ ይኖርበታል::
- ተወዳዳሪዎች አሸናፊ መሆናቸው በፁሁፍ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀን ውስጥ እቃዎቹን ለድርጅቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ስፔሲፊኬሽን በተመለከተ ከድርጅቱ መስሪያ ቤት በመምጣት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ የሰነድ መግዣ 1000 /አንድ ሽ / ብር በመያዝ መግዛት ይቻላል:: ሰነዱን የሚያቀርቡበት መንገድ በአካልም ወይም በፖስታ 1555 ፣ስልክ ቁጥር 0588304550 /0583207068 አድራሻ ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 ሬስ ኢንጅነሪንግ 2ኛ ፎቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን::
- ማሳሰቢያ፦ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ያስገቡት ሰነድ ውድቅ ስለሚደረግበት ሁኔታ፡- 1. የተወዳደሩበትን 2በመቶ ሲፒኦ አለማስያዝ፣ 2. በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሰረት አለማቅረብ ፣3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና EFDA ሰርቲፊኬት አለማቅረብ፣ 4. የማቅረቢያ ቀን ድርጅቱ በተቁ 11 የተገለፀውን የማያሟሉ ሲሆን፡፡ ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻችን ፡- medxdiagnostics2013@gmail.com
ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ