ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
74

ጨረታ ቁጥር አብክመ/ውኢቢ/ግጨ/ዕግ/ቁጥር – 004/2017

በአብክመ የውኃና ኢነርጅ ቢሮ በመንግስት ኢመርጀንሲ የበጀት ድጋፍ ሎት 1.የጠላቂና ሰርፊስ ፓምፕ ዕቃዎች የዕቃ አቅርቦት ግዥ ፣ሎት 2. የቧንቧና መገጣጠሚያ ዕቃዎች የዕቃ አቅርቦት ግዥ እና ሎት 3. የሶላር ዕቃዎች የዕቃ አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ዕቃውን ወይም አገልግሎቶችን ለማቅረብ በዘርፉ (የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች ጅምላ አቅራቢነት) ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር  /ቲን/  ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ  መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሀና ኢነርጅ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00 /አንድ ሽህ  ብር/ በመክፈል  በአብክመ  ውሃና ኢነርጅ ፣ግዥ ፣ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 27 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ለሎት ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/፣ ለሎት 2. ብር150,000 /አንድ መቶ አምሳ ሺህ/  ብር እና ለሎት 3. ብር 300,000.00 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/  የጨረታ ማስከበሪያ  ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከ23/10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15  ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው መዝጊያ ቀን ደግሞ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም መሆኑን  እየገለፅን በዚሁ ቀን 4፡00  ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08  በ4፡30  ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ  የሥራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ ወይም ቅጽ መሰረት መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +25158- 226 -24 60 /+251 582-20-08-55  በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአብክመ  የውኃና ኢነርጅ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here