ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
77

ቁጥር 9

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተለያዩ አገልግሎት የሚዉሉ የአገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የፈለገ ሲሆን ማለትም ፡- 1. ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣2. ያገለገሉ የተለያዩ አላቂ ዕቃዎች 3. ያገለገሉ የተለያዩ ፈርኒቸር ዕቃዎች ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ፣ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104 ሰነዱን በመዉሰድ መወዳደር ይቻላል፡፡
  3. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ም/ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አምስት በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ስፒኦ/ ፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  6. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. የሚሸጡ ዕቃዎች ዓይነት ፣ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here