ማስታወቂያ

0
52

በአፈ/ከሣሽ ዳኛቸው ገሠሠ እና በአፈ/ተከሣሽ አቶ ሠጤ አስራት መካከል ባለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ የጨረታ አሸናፊው አቶ ማስተዋል ገረመው በመራዊ ከተማ ቀበሌ 01 በምሥራቅ ጋሻ ገኔ ፣በደቡብ ወ/ሮ ይታይሽ ፣በምዕራብ እና በሰሜን መንገድ መካከል የሚገኘው ቋሚ ማንጐ አትክልት ብዛት 182 እግር ግምታቸው 10920 /አስር ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ብር/ በመነሻ ተጫርቶ በብር 450‚000.00 /አራት መቶ ሃምሣ ሺህ ብር/ አሸናፊ ስለመሆኑና በቀን 12/08/2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት ትዕዛዝ መሠጠቱ ይታወቃል፡፡ ጨረታው በይግባኝ ተቋርጦ መቆየቱም የሚታወቅ ስለሆነ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት አፈፃፀሙ እንዲቀጥል ያዘዙ ስለሆነ በጨረታው ባሸነፈው መሠረት ንብረቱን ቀርበህ ባለበት ወረዳና ቀበሌ እንድትረከብ ቀርበህ የማትረከብ ከሆነ ግን ፍ/ቤቱ አዲስ ጨረታ የሚያወጣ መሆኑን ለሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here