ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
63

በአማራ ገጠር መንገዶች ኮን/ኤጀንሲ የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ አሮጌ ተመላሽ ጎማ ፣ባትሪ ፣በርሚል ፣ካለመዳሪ እንዲሁም ፍላፕ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት፡- ሎት 1 ያገለገሉ ጎማ ፣ሎት 2 ባትሪ ፣ሎት 3 በርሚል ፣ሎት 4 ካለመዳሪ /ውስጥ ላስቲክ/ እና  ሎት 5 ፍላፕ ስለዚህ፡-

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም አካል በጨረታው መሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ተጫራቾች የንብረቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ቢሮ ቁጥር 19 በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም /ቢድ ቦንድ/ ጠቅላላ ዋጋ 5 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ስም ደረሰኝ በማስቆረጥ ጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች በጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስክ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማየት ይችላሉ፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን /መጫረቻውን/ ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር ከሰኞ እስክ አርብ በሥራ ሰዓት እንዱሁም ቅዳሜ እስከ 6፡30 ከ23/10/2017 ዓ/ም እስከ 08/11/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  7. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ08/11/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ቢሮ ቁጥር 19 ጨረታው ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ሆኖ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ሊሸጥ ከተዘጋጀው የንብረት ወይም የዕቃ ዓይነት ከተገለጸው መጠን ብዛት ቀንሰው መወዳደር አይችሉም ፣ሁሉንም ንብረቶች ማንሳት አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች በመወዳደሪያ ፖስታቸው ላይ ስም ፊርማ ስልክ ቁጥራቸውን መጻፍ አለባቸው፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 891 18 99 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጐጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት

ደ/ማርቆስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here