ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
76

የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/04/2017

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን/ፑል/፣ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጨምሮ ለ2ቱም መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት አመታዊ የቢሮ ህንፃ እና ምድረ ግቢ የጽዳት አገልግሎት እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሀ/ የጽዳት አገልግሎት በጨረታዉ የሚሳተፉ በአነስተኛና ጥቃቅን ኢተርፕራይዝ ተደራጅተዉ ከትምህርትና ስልጠና ተቋም ማስረጋጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ለ/ የተሽከርካሪ መለዋወጫ አቅርበት የሚሣተፋ የባሕር ዳር ከተማ ላይ መደብር ወይም ወኪል መኖሩን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችና የአገልግሎት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የተሽከርካሪ መለዋወጫ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጥቃቀን የድጋፍ ደብዳቤ በማምጣት ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት  ቢሮ ቁጥር 007 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከአነስተኛና ጥቃቅን ኢተርፕራይዝ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን አስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16 ተኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44 /058 220 96 46 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. አዲስ ከተቋቋሙት ኢንተርፕራይዞች ዉጭ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን/ፑል/

ባህርዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here