ለወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ፣ህትመቶች እና የጽህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፡፡
- ንግድ ፈቃዱና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ብር ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበት የስራ (የእቃ) ዋጋ ድምር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ 2 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ቫት በመመሪያው መሰረት ይሰበስባል
- ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ 1 በመቶ በጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከተፈቀደላቸው ባንከ በተመሰከረለት /ሲፒኦ/ በማሲያዝ ከፖስታው ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታ እራሣቸውን ማግለል አይቻልም፡፡
- የጨረታ ሰነድን ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን ግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ከ30/10/2017 ዓ.ም እስከ 20/11/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ለ21 ቀናት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ 20/11/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ በዚህ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በሥራ ሂደቱ ስልክ 033 331 01 72 እና 033 331 02 52 ደወሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- የጨረታ መክፍቻ ቀን በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ተነግሮት ውል ከወሰደ በኋላ ሆስፒታሉ በሚያዘው መሰረት ገዝቶ ማቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውለታ ከወስደበት ቀን ጀምሮ እስከ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ሲታዘዝ ማቅረብ አለበት፡፡
- የተጠቀስውን ግብዓት በጨረታ አሽናፊው ወጭውን ችሎ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
- ወድድሩ በሎት ድምር ነው፡፡
የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል