የአብክመ ፍትህ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት እስከ 30/10/2018 ዓ/ም አጠቃላይ የቢሮና የግቢ ፅዳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻያል በአንድ ፖስታ እና ቴክኒካሉን በሌላ ፖስታ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለቢሮ እና ግቢ ፅዳት ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 30,000 /ሰላሣ ሺህ / ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከ7/11/2017 እስከ 21/11/2017 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀናት ታትሞ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን በ22/11/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል ማግኘት ይቻላሉ፡፡
የአብክመ ፍትህ ቢሮ