የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በ2017 በጀት ዓመት የተመረተዉን በቆሎ ከተከማቸበት ከተማ ወደ ሚፈለገዉ ቦታ ለማጓጓዘ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈፀም፤ በተጨማሪም የሰብል ጥበቃ ኬሚካል፣ የማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ (ኮምፕረሰር)፣ ለመግዛት እና ለምግብነት የሚዉሉ ንፁህ በቆሎ ፣የተበጠረና ያልተበጠረ ንፁህ ጤፍ፣ ንፁህ የተበጠረ ሽምብራ እና ብጣሪዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ከንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም ቢሮ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑን የመንግስት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የመኪና ባሌቤትነት ማረጋገጫ እና የመጫን ችሎታ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት/ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የደረቅ ጭነት ማመላለሻ መኪናዎች ያሉትና የመኪናዎችን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ከዋናው ጋር የተረጋገጠ ኮፒ እንዲሁም ሲጠየቅ ዋናውን ሊብሬ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የባለቤትነት ማረጋገጫው በውክልና በ2017 ዓ.ም የተሰጠ ሆኖ ውክልናው አግባብ ባለው የፍትህ አካል የተረጋገጠ፡፡
- የሚጓጓዘውን ሰብል አይነት፣ መጠን እርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአንድ ሎት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ / ብር በመክፈል ማግኘት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር/10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መስሪያ ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
- የተለያዩ ንፁህ ሰብሎች የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸዉ፡፡
- የተለያዩ ሰብሎችንና ብጣሪን በተመለከተ ንግድ ፈቃድ እንዲያቀርቡ አይገደዱም፡፡
- ግዠዉን ባህር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዘን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ሌሎች ሰብሎችን በተመለከተ ባህር ዳር እና እንጅባራ የሚገኙ ሲሆን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ይመልከቱ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ አለ በጅምላ ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ 10ኛው ቀን ወይም ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ30 ይከፈታል፡፡
- ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582266002 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0583208415/0918016935 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

