ቪሩንጋ ብሔራዊ ፓርክ

0
45

ቪሩንጋ ብሔራዊ ፓርክ በኮንጐ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ምስራቃዊ ቀጣና የሚገኝ ሲሆን በዓለማችን ካሉ በብዝሃ ህይወት ሀብት ታዋቂ ከሆኑ ቀዳሚዎች መካከል ተጠቃሽ ነው::

ፓርኩ በ1925 እ.አ.አ ተመስርቶ በዓለም አቀፍ የአካባቢ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት በ1979 እ.አ.አ ነው የተመዘገበው:: ይህም ከአፍሪካ ቀደምት ፓርኮች ረድፍ አሰልፎታል::

የፓርኩ ክልል በሰሜን የሰሜሊኪ ወንዝ ተፋሰስን እና የአልበርቲን ሸለቆ ደን ያጠቃልላል:: የመገኛው ከፍታ አነስተኛው 680 ሜትር ከፍተኛው የስታንሊ  ተራራ 5109 ሜትር ተለክቷል:: ደቡባዊው ቀጣና የኪቡ ኃይቅ፣ ኒራጎንጎ እና ማይካኖ የመሳሰሉ በእሳተገሞራ የተፈጠሩ ሳር ለበስ ተራራዎችን አካቷል::

በአየር ንብረቱ ከ23 እስከ 28  ዲግሪ ሴልሺየስ የተመዘገበ ሲሆን ከመጋቢት እስከ ግንቦት አጋማሽ እና ከመስከረም እስከ ህዳር የዝናብ ወራቶች ናቸው:: አማካይ የወሩ ከ30 እስከ 40 ሚሊሜትር ተለክቷል በደረቅ ወራት፤ በዝናባማው ወራት ደግሞ 220 ሚሊሜትር በአማካይ ያገኛል::

በቪሩንጋ ብሔራዊ ፓርክ 2077 የእፅዋት ዝርያዎች ይገኛሉ:: በተራራማ አቀበት እና አናት 264 የዛፍ ዝርያዎች፤ 230 ዎቹ ደግሞ በዝቅተኛ ሸለቆ የሚገኙ የእፅዋት ዝርያ  መሆናቸው ተረጋግጧል::

በዱር እንስሳት 196 አጥቢ፣ 706 የአእዋፍ ዝርያዎች፣ 109 ተሳቢ እና 65 የውኃ ውስጥ እንስሳት መኖራቸውም ተለይቷል::

በሳር ለበሱ ሜዳማ የፓርኩ ቀጣና በኮንጐ ብቻ የሚገኘው (okapi) የተሰኘው (ብር ቅዬ) ሳላ መሰል እንስሳት መገኛ ነው::  ሳር ለበሱ የፓርኩ ቀጣና አቅፎ በያዘው ብዝሃ ህይወት ማለትም በእፅዋት እና እንስሳት ሀብቱ በቀዳሚነት ተጠቃሽ መሆኑንም ነው ድረ ገፆች ያስነበቡት::

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ደብሊው ኤችሲ፣ ዩኔስኮ፣ ቪሩንጋ፣ ቪዚት ቪሩንጋ ድረገፆችን ተጠቅመናል::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here